አዋጅ ቁጥር ፹፩/፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ከባድ ድርቅ እና/ወይም በረሃማነት በሚያጠቃቸው አገሮች፣ በተለይም በአፍሪካ ውስጥ በረሃማነትን የመከላከል ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማጽደቂያ አዋጅ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

አዋጅ ቁጥር ፹፩/፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ከባድ ድርቅ እና/ወይም በረሃማነት በሚያጠቃቸው አገሮች፣ በተለይም በአፍሪካ ውስጥ በረሃማነትን የመከላከል ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማጽደቂያ አዋጅ

አዋጅ ቁጥር ፹፩/፲፱፻፹፱
ከባድ ድርቅ እና/ወይም በረሃማነት በሚያጠቃቸው
አገሮች፣ በተለይም በአፍሪካ ውስጥ በረሃማነትን
የመከላከል ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንን ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ

ከባድ ድርቅ እና/ወይም በረሃማነት የሚያጠቃቸው አገሮች፣ በተለይም በአፍሪካ ውስጥ በረሃማነትን የመከላከል ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽንን እ.ኤ.አ ኦክቶበር ፲፭ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. በፓሪስ ከተማ በኢትዮጵያም የተፈረመ ስለሆነ፤
ኮንቬንሽኑ በሥራ ላይ የሚውለው ከሃምሣ ሀገሮች የማጽደቂያ ሰነዶች ቀርበው ከተመዘገቡበት ጊዜ ከጠዘነኛው ቀን ጀምሮ እንደሚሆን በኮንቬንሽኑ ውስጥ የተመለከተ ስለሆነ፤
ይህንኑ ስምምነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰኔ ፲፯ ቀን ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭  ንዑስ አንቀጽ (፩) እና (፲፪) መሠረት ከዚህ እንደሚከተለው ታውጇል፡፡

፩. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ ‹‹ከባድ ድርቅ እና/ወይም በረሃማነት በሚያጠቃቸው አገሮች፣ በተለይም በአፍሪካ ውስጥ በረሃማነትን የመከላከል ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር ፹፩/፲፱፻፹፱›› ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ኮንቬንሽኑ ስለመጽደቁ
እ.ኤ.አ ኦክቶበር ፲፭ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. በፓሪስ የተፈረመው ከባድ ድርቅ እና/ወይም በረሃማነት በሚያጠቃቸው አገሮች፣ በተለይም በአፍሪካ ውስጥ በረሃማነትን የመከላከል ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ጸድቋል፡፡

፫. የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ሥልጣን
የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አግባብ ካላቸው የፌዴራልና የክልል መንግሥታዊ አካላት፣ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች እንዲሁም ከኅብረተሰቡ ጋር በመተባበር ኮንቬንሽኑ በሥራ ላይ እንዲውል የማድረግ ሥልጣን በዚህ አዋጅ ተሰጥቶታል፡፡

፬. አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ ከሰኔ ፲፯ ቀን ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ ፲፯ ቀን ፲፱፻፹፱ ዓ.ም.
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት