አዋጅ ቁጥር ፶፬/፲፱፻፹፱ዓ.ም. የተሻሻለው የሎሜ አራት ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

አዋጅ ቁጥር ፶፬/፲፱፻፹፱ዓ.ም. የተሻሻለው የሎሜ አራት ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ

አዋጅ ቁጥር ፶፬/፲፱፻፹፱
የተሻሻለውን የሎሜ አራት ስምምነት ለማጽደቅ
የወጣ አዋጅ

የተሻሻለውን የሎሜ አራት ስምምነት ኢትዮጵያ እና የተቀሩት ወገኖች እ.ኤ.አ. ኖቬምበር ፬ ቀን ፲፱፻፺፭ ሞሪሽየስ ላይ ስለተፈራረሙ፤
ስምምነቱ በሥራ ላይ የሚውለው በተፈራራሚዎቹ ሀገሮች ሲጸድቅ በመሆኑ፤
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሻሻለውን ስምምነት ታህሳስ ፰ ቀን ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ፣
በሕገመንግሥቱ አንቀጽ ፶፭ ንዑስ አንቀጽ (፩) እና (፲፪) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

፩. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ ‹‹የተሻሻለው የሎሜ አራት ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር ፶፬/፲፱፻፹፱›› ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ስምምነቱ ስለመጽደቁ
እ.ኤ.አ ኖቬምበር ፬ ቀን ፲፱፻፺፭ ሞሪሽየስ ላይ የተፈረመው የተሻሻለ የሎሜ አራት ስምምነት ጸድቋል፡፡

፫. የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴር ሥልጣን
የኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴር አግባብ ካላቸው የመንግሥትና የግል አካላት ጋር በመተባበር የተሻሻለው የሎሜ አራት ስምምነት በሥራ ላይ እንዲውል የማድረግ ሥልጣን በዚህ አዋጅ ተሰጥቶታል፡፡

፬. አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ ከታኅሣሥ ፰ ቀን ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ ታኅሣሥ ፰ ቀን ፲፱፻፹፱ ዓ.ም.
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት