አዋጅ ቁጥር ፶፩/፲፱፻፹፱ ዓ.ም. የመንግሥት ቤቶች ሽያጭ አስፈጻሚ ጽሕፈት ቤት ማቋቋሚ (ማሻሻያ) አዋጅ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

አዋጅ ቁጥር ፶፩/፲፱፻፹፱ ዓ.ም. የመንግሥት ቤቶች ሽያጭ አስፈጻሚ ጽሕፈት ቤት ማቋቋሚ (ማሻሻያ) አዋጅ

አዋጅ ቁጥር ፭፩/፲፱፻፹፱
የመንግሥት ቤቶች ሽያጭ አስፈጻሚ ጽሕፈት ቤትን
ማቋቋሚያ አዋጅ
ለማሻሻል የወጣ አዋጅ

የመንግሥት ቤቶች ሽያጭ አስፈጻሚ ጽሕፈት ቤትን ማቋቋሚያ አዋጅ እንደገና ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭(፩) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

፩. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ ‹‹የመንግሥት ቤቶች ሽያጭ አስፈጻሚ ጽሕፈት ቤት ማቋቋሚያ (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር ፶፩/፲፱፻፹፱›› ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ማሻሻያ
የመንግሥት ቤቶች ሽያጭ አስፈጻሚ ጽሕፈት ቤት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፻፲፪/፲፱፻፹፯ (እንደተሻሻለ) እንደሚከተለው እንደገና ተሻሽሏል፡፡
፩. ከአንቀጽ ፱ ንዑስ አንቀጽ (፬) ቀጥሎ የሚከተለውን አዲስ ንዑስ አንቀጽ (፭) ተጨምሯል፤
‹‹፭. የጽሕፈት ቤቱን መዋቅርና የጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞች የሚተዳደሩበትን የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን መሠረታዊ ዓላማዎች ተከትሎ የተዘጋጀ መመሪያ ያጸድቃል፡፡››
፪. የአንቀጽ ፱ የቀድሞዎቹ ንዑስ አንቀጽ (፭) እና (፮) እንደቅደም ተከተላቸው ንዑስ አንቀጽ (፮) እና (፯) ሆነዋል፡፡
፫. በአንቀጽ ፲፩ ንዑስ አንቀጽ (፪)(ሐ) ውስጥ ‹‹በመንግሥት ሠራተኞች ሕግ መሠረት›› የሚለው ሐረግ ተሰርዞ ‹‹ቦርዱ ባጸደቀው መመሪያ መሠረት›› በሚለው ተተክቷል፡፡

፫. አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ ከኅዳር ፳፮ ቀን ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ ኅዳር ፳፮ ቀን ፲፱፻፹፱ ዓ.ም.
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት