አዋጅ ቁጥር ፬፻፷፮/፲፱፻፺፯ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

አዋጅ ቁጥር ፬፻፷፮/፲፱፻፺፯ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ

አዋጅ ቁጥር ፬፻፷፮/፲፱፻፺፯
የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅን ለማሻሻል
የወጣ አዋጅ

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር ፫፻፸፯/፲፱፻፺፮ን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ /፩/ እና /፫/ መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

፩. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ “የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ /ማሻሻያ/ አዋጅ ቁጥር ፬፻፷፮/፲፱፻፺፯” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ማሻሻያ
የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ አዋጅ ቁጥር ፫፻፸፯/፲፱፻፺፮ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፤
፩. የአዋጁ አንቀጽ ፻፵፬ /ንዑስ አንቀጽ /፩/ እና /፪/ ተሰርዘው በሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጽ /፩/ እና /፪/ ተተክቷል፤
“፩. በእያንዳንዱ ክልል ውስጥ እንደአስፈላጊነቱ አንድ ወይም ከአንድ በላይ ቋሚ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ /ከዚህ በኋላ ቋሚ ቦርድ እየተባለ የሚጠራ/ ሊቋቋም ይቻላል፡፡ ሆኖም በአዲስ አበባ ከተማ በፌዴራል መንግሥት ሥር የሚተዳደሩ ድርጅቶችን ጉዳይ የሚያይና የሚወስን ቦርድ ለበቻ ይቋቋማል፡፡
፪. በእያንዳንዱ ክልል በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፻፴፮/፪/ በተመለከቱ ድርጅቶች በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፻፵፪ ፩/ሀ/ ላይ የሚነሳን ጉዳይ ለማየትና ለመወሰን ሥልጣን ያለው ጊዜያዊ የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ /ከዚህ በኋላ ጊዜያዊ ቦርድ ተብሎ የሚጠራ/ሊቋቋም ይቻላል፡፡ ሆኖም በአዲስ አበባ ከተማ ድርጅቶችን ጉዳይ የሚያይና የሚወሰነው ጊዜያዊ ቦርድ ለብቻ ይቋቋማል፡፡
፪. በአዋጁ አንቀጽ ፻፵፬ ሥር የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ /፬/ተጨምሮአል፤
“፬. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /፫/ ድንጋጌ ቢኖርም በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ /፩/ እና /፪/ የተመለከቱት በፌዴራል መንግሥት ሥር የሚተዳደሩ ድርጅቶችን ጉዳይ የሚያዩና የሚወስኑ ቋሚና ጊዜያዊ ቦርዶች በሠራተኛና ማኀበራዊ ጉደይ ሚኒስቴር ሥር ይሆናሉ፡፡”

፫. አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳፫ ቀን ፲፱፻፺፯ ዓ.ም. ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ ሰኔ ፳፫ ቀን ፲፱፻፺፯ ዓ.ም.
ግርማ ወልደጊዮርጊስ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ
ራፐብሊክ ፕሬዚዳንት