አዋጅ ቁጥር አዲስ ፬፻፷፭/፲፱፻፺፯ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ለማሻሻል የወጣ አዋጅ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

አዋጅ ቁጥር አዲስ ፬፻፷፭/፲፱፻፺፯ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ለማሻሻል የወጣ አዋጅ

አዋጅ ቁጥር አዲስ ፬፻፷፭/፲፱፻፺፯
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ
አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ
ለማሻሻል የወጣ አዋጅ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣውን አዋጅ ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ ፶፭ /፩/ መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡
፩. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ “የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ /ማሻሻያ/ አዋጅ ቁጥር ፬፻፷፭/፲፱፻፺፯” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ማሻሻያ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር ፬/፲፱፻፹፯ / /እንደተሻሻለ/ አንቀጽ ፳፫ ንዑስ አንቀጽ /፱/ ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ /፱/ ተተክቷል፤
“፱. ዓላማቸው ትርፍ ማግኘት ያልሆኑ የውጭ ድርጅቶችን እንዲሁም እንቅስቃሴያቸው በአዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተሞች የሆነ ወይም አንድ ክልል ያልወሰነ የአገር ውስጥ ድርጅቶችንና ማኀበሮችን ይመዘግባል፤”

፫. አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳፫ ቀን ፲፱፻፺፯ ዓ.ም. ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ ሰኔ ፳፫ ቀን ፲፱፻፺፯ ዓ.ም.
ግርማ ወልደጊዮርጊስ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ
ራፐብሊክ ፕሬዚዳንት