አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፪/፲፱፻፺፫ ዓ.ም. የአፍሪካ ሕብረትን ለማቋቋም የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፪/፲፱፻፺፫ ዓ.ም. የአፍሪካ ሕብረትን ለማቋቋም የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ

አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፪/፲፱፻፺፫ ዓ.ም.
የአፍሪካ ሕብረትን ለማቋቋም የተደረገውን ስምምነት
ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ

የአፍሪካ ሕብረትን ማቋቋሚያ ስምምነት ኢትዮጵያና የተቀሩት የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አባል አገሮች እ.ኤ.አ ጁላይ ፲፩ ቀን ፪ሺ ሎሜ ላይ ስለተፈራረሙ፤
ስምምነቱ በሥራ ላይ የሚውለው ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት አባል አገሮች ሁለት ሦስተኛው የስምምነቱ ማጽደቂያ ሰነዶቻቸውን ከአፍሪካ አንድነት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ዘንድ ተቀማጭ ካደረጉበት ጀምሮ ከ፴ ቀናት በኋላ እንደሚሆን በስምምነቱ ውስጥ የተመለከተ ስለሆነ፤
ይህንኑ ስምምነት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት ፳፱ ቀን ፲፱፻፺፫ ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ያፀደቀው በመሆኑ፤
በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ ፶፭ (፩) እና (፲፪) መሠረት ከዚህ እንደሚከተለው ታውጇል፡፡

፩. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ ‹‹የአፍሪካ ሕብረት ማቋቋሚያ ስምምነት ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር ፪፻፴፪/፲፱፻፺፫›› ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ስምምነቱ ስለመጽደቁ
እ.ኤ.አ. ጁላይ ፲፩ ቀን ፪ሺ ሎሜ ላይ የተፈረመው የአፍሪካ ሕብረት ማቋቋሚያ ስምምነት ጸድቋል፡፡

፫. አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ ከየካቲት ፳፱ ቀን ፲፱፻፺፫  ዓ.ም ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ የካቲት ፳፱ ቀን ፲፱፻፺፫ ዓ.ም.
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ
ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት