አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፰/፲፱፻፺፫ ዓ.ም. የሽያጭና ኤክሳይዝ ታክስ አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፰/፲፱፻፺፫ ዓ.ም. የሽያጭና ኤክሳይዝ ታክስ አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ

አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፰/፲፱፻፺፫ ዓ.ም.
የሽያጭና ኤክሳይዝ ታክስ አዋጅን ለማሻሻል
የወጣ አዋጅ

የሽያጭና ኤክሳይዝ ታክስ አዋጅን ማሻሻል በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭(፩) እና (፲፩) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

፩. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ ‹‹የሽያጭና ኤክሳይዝ ታክስ (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፲ ›› ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ማሻሻያ
የሽያጭና ኤክሣይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር ፷፰/፲፱፻፹፭ (እንደተሻሻለ) እንደገና እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡፡
የአዋጁ አንቀጽ ፭ ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፭ ተተክቷል፤
‹‹ ፭ የሽያጭ ታክስ ተመን
፩. ከዚህ አዋጅ ጋር በተያያዘው ሠንጠረዥ ‹‹ሀ›› ውስጥ በተመለከቱት በአገር ውስጥ በሚሸጡ እና ከውጭ አገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ እንደአግባብነቱ ፭% (አምስት በመቶ) ወይም በቁርጥ በመለኪያ፤
፪. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) እና በሠንጠረዥ ‹‹ለ›› ከተመለከቱት በስተቀር በሌሎች በማናቸውም በአገር ውስጥ በሚሸጡ እና ወደአገር በሚገቡ ዕቃዎች ላይ ፲፭% (አሥራ አምስት በመቶ)
፫. በአገር ውስጥ በሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ፤
ሀ) ማናቸውም የሥራ ተቋራጮች እንዲሁም የፋይናንስ አገልግሎቶች ፭% (አምስት በመቶ)፡፡
ለ) ሌሎች ፲፭% (አሥራ አምስት በመቶ)

፫. አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ ከታህሣሥ ፳፮ ቀን ፲፱፻፺፫ ዓ.ም ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡
አዲስ አበባ ታህሣሥ ፳፮ ቀን ፲፱፻፺፫ ዓ.ም.

ዶር ነጋሶ ጊዳዳ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ፕሬዚዳንት