አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፮/፲፱፻፺፫ የነዳጅ ሥራዎች ገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፮/፲፱፻፺፫ የነዳጅ ሥራዎች ገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ

አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፮/፲፱፻፺፫
የነዳጅ ሥራዎች ገቢ ግብር አዋጅን ለማሻሻል
የወጣ አዋጅ

የነዳጅ ሥራዎች ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር ፪፻፺፮/፲፱፻፸፰ን ማሻሻል በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ ፶፭ (፩) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

፩. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ ‹‹የነዳጅ ሥራዎች ገቢ ግብር (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር ፪፻፳፮/፲፱፻፺፫›› ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ማሻሻያ
የነዳጅ ሥራዎች ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር ፪፻፺፮/፲፱፻፸፰ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፤
፩. የአዋጁ አንቀጽ ፫ ንዑስ አንቀጽ (፩) ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ (፩) ተተክቷል፤
፩. በነዳጅ ስምምነት መሠረት የነዳጅ ሥራዎች የሚያካሂድ ማንኛውም ሰው ግብር ከሚከፍልበት ገቢው ላይ ፴ በመቶ (ሠላሳ ፐርሰንት) የገቢ ግብር ይከፍላል፡፡››
፪. የአዋጁ አንቀጽ ፲፫ ንዑስ አንቀጽ ፮ (ሀ) ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ ፮ (ሀ) ተተክቷል፤
ሀ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) እና (፪) መሠረት ከሚሰላው የሰብ ኮንትራክተሩ ግብር የሚከፈልበት ገቢ ላይ ሰብኮንትራክተሩ ፴ በመቶ (ሠላሳ ፕርሰንት) ተመን መክፈል ያለበትን የግብር ክፍያ ይቀንሳል፡፡››
፫. የአዋጁ አንቀጽ ፲፭ ተሠርዟል፡፡
፬. የአዋጁ አንቀጽ ፲፮፣ ፲፯፣ ፲፰ እና ፲፱ እንደቅደም ተከተላቸው አንቀጽ ፲፭፣ ፲፮፣ ፲፯ እና ፲፰ ሆነዋል፡፡

፫. አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ ከታህሣሥ ፲፯ ቀን ፲፱፻፺፫ ዓ.ም ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡
አዲስ አበባ ታህሣሥ ፲፯ ቀን ፲፱፻፺፫ ዓ.ም

ዶር ነጋሶ ጊዳዳ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ፕሬዚዳንት