አዋጅ ቁጥር ፩፻፺፪/፲፱፻፺፪ ዓ.ም. የአደገኛ ዝቃጮች ድንበር ዘለል ዝውውርን እና አወጋገድን ለመቆጣጠር የወጣውን የባዝል ኮንቬንሽን ማጽደቂያ አዋጅ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

አዋጅ ቁጥር ፩፻፺፪/፲፱፻፺፪ ዓ.ም. የአደገኛ ዝቃጮች ድንበር ዘለል ዝውውርን እና አወጋገድን ለመቆጣጠር የወጣውን የባዝል ኮንቬንሽን ማጽደቂያ አዋጅ

አዋጅ ቁጥር ፩፻፺፪/፲፱፻፺፪
የአደገኛ ዝቃጮች ድንበር ዘለል ዝውውርን እና አወጋገድን ለመቆጣጠር የወጣውን የባዝል ኮንቬንሽን ለማጽደቅ የወጣ አዋጅ

የአደገኛ ዝቃጮች ድንበር ዘለል ዝውውርን እና አወጋገድን ለመቆጣጠር የወጣውን የባዝል ኮንቬንሽን እ.ኤ.አ. ማርች ፳፪ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. የወጣ ስለሆነ፣
ይህንኑ ኬንቬንሽን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት ፪ ቀን ፲፱፻፺፪ ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ያጽደቀው ስለሆነ፣
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ  ፶፭(፩) እና (፲፪) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

፩. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ “የአደገኛ ዝቃጮች ድንበር ዘለል ዝውውርን እና አወጋገድን ለመቆጣጠር የወጣውን የባዝል ኮንቬንሽን ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር ፩፻፺፪/፲፱፻፺፪” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ኮንቬንሽኑ ስለመጽደቁ
የአደገኛ ዝቃጮች ድንበር ዘለል ዝውውርን እና አወጋገድን ለመቆጣጠር እ.ኤ.አ. ማርች ፳፪ ቀን ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. የወጣው የባዝል ኮንቬንሽን ጽድቋል፡፡

፫. የአካባቢ ጥበቃ ባልሥልጣን ኃላፊነት
የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አግባብ ካላቸው የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ መስተዳድር የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጋር በተመባበር ኮንቬንሽኑ በሥራ ላይ እንዲውል የማድረግ ኃላፊነት በዚህ አዋጅ ተሰጥቶታል፡፡

፬. አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ ከየካቲት ፪ ቀን  ፲፱፻፺፪ ዓ.ም. ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ የካቲት ፪ ቀን ፲፱፻፺፪ ዓ.ም.
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት
የኢትየጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ
ስድስተኛ ዓመት ቁጥር ፳፩ አዲስ አበባ የካቲት ፳፰ ቀን ፲፱፻፺፪
በኢትየጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠባቂነት የወጣ