አዋጅ ቁጥር ፻፳፪/፲፱፻፺ ዓ.ም. የብሔራዊ ዕፅዋት ዘር ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ (ማሻሻያ) አዋጅ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

አዋጅ ቁጥር ፻፳፪/፲፱፻፺ ዓ.ም. የብሔራዊ ዕፅዋት ዘር ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ (ማሻሻያ) አዋጅ

አዋጅ ቁጥር ፻፳፪/፲፱፻፺
ብሔራዊ የዕፅዋት ዘር ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ

ብሔራዊ የዕፅዋት ዘር ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ አዋጅን ማሻሻል በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ፶፭ (፩) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

፩. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ “የብሔራዊ ዕፅዋት ዘር ኢንዲስትሪ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር ፻፳፪/፲፱፻፺” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ማሻሻያ
የብሔራዊ የዕፅዋት ዘር ኢንዱስትሪ ኤጀንሲ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፶፮/፲፱፻፹፭ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡፡
፩. የአዋጁ አንቀጽ ፱ ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፱ ተተክቷል፡፡
“፱. የቦርዱ አባላት
ቦርዱ ሰብሳቢውን ጨምሮ በመንግሥት የሚሰየሙ ቁጥራቸው እንዳስፈላጊነቱ የሚወሰን አባላት ይኖሩታል፡፡››
፪. በአዋጁ ውስጥ በማናቸውም ሥፍራ “ምክር ቤት” የሚለው ስያሜ “ቦርድ” ተብሎ ይነበባል፡፡

፫. አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ ከሰኔ ፳፫ ቀን ፲፱፻፺ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት