አዋጅ ቁጥር ፻፲፰/፲፱፻፺ ዓ.ም. የማዕድን (ማሻሻያ) አዋጅ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

አዋጅ ቁጥር ፻፲፰/፲፱፻፺ ዓ.ም. የማዕድን (ማሻሻያ) አዋጅ

አዋጅ ቁጥር  ፻፲፰/፲፱፻፺
የማዕድን አዋጅን ለማሻሻል የወጣ አዋጅ
የማዕድን አዋጅን ማሻሻል በማስፈለጉ፤
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ ፶፭(፩) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

፩. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ “የማዕድን (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር ፻፲፰/፲፱፻፺” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ማሻሻያ
የማዕድን አዋጅ ቁጥር ፶፪/፲፱፻፹፭ እንደሚከተለው ተሻሽሏል፡፡
፩. የአዋጁ አንቀጽ ፵ ሙሉ በሙሉ ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፵ ተተክቷል፤
“፵. የመሬት ኪራይን በሚመለት ይህ ማሻሻያ አዋጅ ከመውጣቱ በፊት በማዕድን ስምምነት ውስጥ ከኢንቨስተሩ (ከባለሀብቱ) ጋር ስምምነት የተደረሰባቸው የኪራይ ተመኖች በውሉ መሠረት የኪራይ ዘመኑ እስከሚጠናቀቅበት ድረስ እንደተጠበቁ ይሆናሉ፡፡”
፪. የአዋጁ አንቀጽ ፵፮ ንዑስ አንቀጽ (፩) እንደተሻሻለ እንደገና በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ (፩) ተሻሽሏል፡፡
“(፩) የብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድሮች ለባሕላዊ የማዕድን ማምረት ሥራዎች እና በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች ብቻ ለሚካሄዱ የፍለጋ፣ የምርመራ፣ አነስተኛ የማዕድናት ፈቃድ የመስጠት ሥልጣን የተሰጣቸው ሲሆን ለሌሎች ማናቸውም የማዕድን ሥራዎች ፈቃድ ሲሆን ሚኒስቴሩ ፈቃድ የሚሰጠው በቅድሚያ ከሚኒስትሮች ምክር ቤት መመሪያ በመጠየቅ ይሆናል፡፡”
፫. የአንቀጽ ፵፮ ንዑስ አንቀጽ (፪) (ረ) ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀጽ (፪) (ረ)  ተተክቷል፡፡
‹‹ረ. ሚኒስቴሩ ከከፍተኛ ማዕድን ሥራዎች የሚገኝ ሮያሊቲና ሌሎች ክፍያዎች የመሰብሰብና ኦዲት የማድረግ ሥልጣን ይኖረዋል፡፡››

፫. አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ ከሰኔ ፲፮ ቀን ፲፱፻፺ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ፕሬዚዳንት