አዋጅ ቁጥር ፻፪/፲፱፻፺ የኢትዮጵያ የጥሪትና የደረጃዎች ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

አዋጅ ቁጥር ፻፪/፲፱፻፺ የኢትዮጵያ የጥሪትና የደረጃዎች ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ

አዋጅ ፻፪/፲፱፻፺
የኢትዮጵያ የጥራትና የደረጃዎች ባለሥልጣንን ለማቋቋም የወጣ
አዋጅ

የኢኮኖሚ ልማትንና ቴክኖሎጂን በማሻሻል የኅብረተሰቡን አኗኗር ለማበልጸግ የሚደረገው እንቅስቃሴ የጥራትን የሜትሮሎጂንና የደረጃዎች ሥራን ማስፋፋትና መተግበርን አስፈላጊ ስለሚያደርገው፣
በዚህ ረገድ የሚወሰዱ እርምጃዎችን ይበልጥ ለማጠናከር የደረጃዎችንና የጥራት ማስፋፋት ሥራ ኃላፊነት የተጣለሰትን መንግሥታዊ አካል እንደገና ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት አንቀጽ ፶፭/(፩) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

፩. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ “የኢትዮጵያ የጥራትና የደረጃዎች ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፻፪/፲፱፻፺” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፣
፩. “የጥራት ማስፋፋት” ማለት በየደረጃው በሚገኝ የምርት ሂደት ላይ በተመጣጠነ የሀብት አጠቃቀም የጥራት ተፈላጊ ሁኔታወችንና ዓላማዎችን በማሟላት፤ የአንድን ድርጅት ብቃት ለማሳደግና ለማሻሻል የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ ነው፣
፪. “ጥራት” ማለት በቀጥታ የተገለጸንና በተዘዋዋሪ መንገድ የተመለከተን ፍላጎት የማሟላት ችሎታውን የሚገልጽ የአንድ አካል አጠቃላይ ባሕርይ ነው፤
፫. “የደረጃዎች ሥራ” ማለት ደረጃዎች የማዘጋጀት፣ አሳትሞ የማውጣትና የመተግበር ሂደቶችን የሚያካትት እንቅስቃሴ ነው፣
፬. “ደረጃ” ማለት ምርቶች ለታቀዱበት ዓላማ የሚስማሙ መሆናቸውን ለማረጋገጠ እንደ ደንብ መመሪያ ወይም እንደ ባህሪያት ትርጓሜ በቋሚነት ለማገልገለ ቴክኒካዊ ዝርዝር ሁኔታዎችን ወይም ሌሎች መመዘኛዎችን በተመለከተ በስምምነት የተዘጋጀ ሰነድ ነው፣
፭. “ምርት” ማለት የእንቅስቃሴዎች ወይም የሂደቶች ውጤት ሲሆን ይህም አገልግለት ሀርድዌር ሶፍትዌር ፕሮሴስድ ዕቃዎች ወይመ የእነዚህን ጥምር ሊያጠቃልል ይችላል፣
፮. “ሂደት” ማለት ግብአትን ወደ ውጤት የሚለውጥ የተቀናበረ የሀብትና የእንቅስቃሴዎች ጥምር ነው፣
፯. “የኢትዮጵያ ደረጃ” ማለት ማንኛውም ባለሥልጣኑ አጽድቆ የሢያወጣው ደረጃ ነው፣
፰. “ዓለም አቀፍ የአሀዶች ሥርዓት (ኤስአይ)” ማለት የሚዛንና መስፈሪያ ጠቅላላ ኮንፈረንስ (ሲ.ጂ.መ.ኤም) የተቀበለውና በሥራ ላይ እንዲውል ድጋፍ የተሰጠበት የተቀናጀ የአሀዶች ሥርዓት ነው፣
፱. “ኢታሎን” ማለት አንድን አሀድ ወይመ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ የመጠን እሴትን ለመወሰን በተግባር ለመግለጽ ለመጠበቅ ወይም ለመቅዳት የተመደበ መሠረታዊ መለኪያ የመለኪያ መሣሪያ የማመሳከሪያ ስረት ወይም የአለካክ ቅንብር ነው፣
፲.”የተመሰከረለት ማመሳከሪያ ስረት” ማለት የምስክር ወረቀት ያለው የአንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ የባሕሪዩ እሴቶች የተረጋገጡበት ሥርዓት ባህሪዩ የተገለጸበትን አሀድ በተዋረድነት በትክክል የሚገልጽ ሆኖ የእያንዳንዱ የተረጋገጠ እሴት እርግጠኛ አለመሀን በተወሰነ አስተማማኝነት ደረጃ የተገለጸ የማመሳከሪያ ስረት ነው፣
፲፩. “የመለኪያ መሣሪያ” ማለት ብቻውን ወይም ከአጋዥ መማሪያዎች ጋር በመጣመር መጠኖችን ለመለካት እንዲያ ገለግል ታቅዶ የተሠራ መሣሪያ ነው፣
፲፪. “የተስማሚነት ምስክር ወረቀት” ማለት አንድን በሚገባ የተገለጸን ምርት ወይም ሂደት ከተወሰነ ደረጃ ጋር ለመስማማቱ በቂ ማረጋገጫ የሚሰጠ ሰነድ ነው፣
፲፫. “የተስማሚነት ምዘና ሥርዓት” ማለት የራጹ የሀነ የአሰራር ደንብና የማኔጅመንት ዘይቤ ኖሮት አግባብነት ያላቸው የደረጃ ተፈላጊ ሁኔታዎች መሟላታቸውን ለመወሰን በቀጥታና ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን የሚያካትት ሥርዓት ነው፣
፲፬. “ስምምነት” ማለት መሠረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በዋናነት ከሚመለከታቸው ወገኖች ያለማቋረጥ የሚነሳ ተቃውሞ የሌለበት ሆኖ፣ የሁሉንም ወገን ሃሣብ በማስተናገድና የሚጋጩ ሃሳቦችን ለማስታረቅ በመፈለግ ላይ የተመሠረተ አጠቃላይ መግባባት ነው፣
፲፭. “ሰው” ማለት ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው፡፡

፫. እንገና መቋቋም
፩. የኢትዮጵያ የጥራትና የደረጃዎች ባሥልጣን (ከዚህ በኋላ “ባለሥልጣኑ” እየተባለ የሚጠራ) ራሱን የቻለና ሕጋዊ ሰውነት ያለው የፌዴራል መንግሥት አካል ሆኖ በዚህ አዋጅ እንደገና ተቋቁሟል፡፡
፪. ባለሥልጣኑ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል፡፡

፬. ዋና መሥሪያ ቤት
የባለሥልጣኑና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈላጊነቱም ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶች ሊያቋቁም ይችላል፡፡

፭. ዓላማ
ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፣
፩. በማኅበሪዊውና በኢኮኖሚው ዘርፍ የጥራት ሥራ አመራር ልምድ ከሌሎች የሥራ አመሪር ተግባራት ጋር በቅንጅትና እራሱን የቻለ ሆኖ የሚመሰረትበትን ሁኔታ ማስፋፋትና መርዳት፣
፪. የኢትዮጵያ ደረጃዎችን በማስፋፋትና በመተግበር የምርቶችራንና የሂደቶች ጥሪት እንዲሻሻል መርዳት፣
፫. በአገሪቱ ውስጥ በሁሉም ደረጃ የደረጃዎች ሥራን ማስፋፋትና ማስተባበር፣
፬. ለኢኮኖሚ እድገት እንደ መሠረታዊ መዋቅር ሆኖ የሢያገለግል አስተማማኝ የሆነ ብሔራዊ የሜትሮሎጂ ሥርዓት ማቋቋም፣
፭. በአገር አቀፍ ደረጃ አስተማማኝነት ያላቸው የፍተሻ ላቦራቶሪዎች እንዲስፋፉ፣ እንዲጠናከሩና እንዲጐለብቱ ማድረግ፡፡

፮. ሥልጣንና ተግባር
ባለሥልጣኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባሮች ይኖሩታል፣
፩. የኢትዮጵያ ደረጃዎችን በብቸኝነት ማጽደቅና ማሳወቅ እንዲሁም ብሔራዊ ኢታሎኖችን መጠበቅ፣
፪. እንደአስፈላጊነቱ ለአጠቃላይ ወይም በተለይ ለተወሰነ አገልግሎት የኢትዮጵያ ደረጃዎችን ማዘጋጀት ማጽደቅ ማስታወቅና አሳትሞ ማውጣት፣
፫. በብሔራዊ አህጉራዊ ወይም ዓለም አቀፍ የደረጃዎች ሥራን በሚያከናውኑ አካላት የተዘጋጀን ማንኛውንም ደረጃ እንደ አስፈላጊነቱ እንደ ኢትዮጵያ ደረጃ እውቅናን መስጠት፣
፬. ከገሪቱ የልማት መርሃ ግብር ጋር የተጣጠመ የጥራት ማስፋፋት የደረጃ ምደባ ፖሊስና ስትራቴጂ ማዘጋጀትና ሲፈቀድም ተግባራዊ ማድረግ አፈጻጸሙንም መከታተል፣
፭. አስተማማኝ የሆነ ብሔራዊ የሜትሮሎጂ ሥርዓትን ለማቋቋም፣
ሀ. ብሔራዊ ኢታሎኖችንና የተመሰከረላቸው ማመሳከሪያ ስረቶችን መጠበቅና ማሰራጨት፣
ለ. የዓለም አቀፍ አሀዶች ሥርዓትን (ኤስ.አይ.) የፊዚካል መጠኖች መለኪያ እንደ ብቸኛ የአለካክ ሥርዓት ማስተዋወቅ፣
ሐ. የመለኪያ መሣሪያዎችን ትክክለኝነት ማረጋገጥ እና/ወይም ካሊብሬት ማድረግ፣
፮. ብሔራዊ የተስማሚነት ምዘና ሥርዓትን ማቋቋምና በሥራ ላይ ማዋል፣
፯. ምርቶች አግባብነት ካላቸው ተፈላጊ ሁኔታዎች ጋር መስማማታቸውን ለማረጋገጥ፣ የኢንዱስትሪና የእርሻ ምርምሮችን ለመርዳትና በአገሪቱ ውስጥ በሁሉም ደረጃ ለሚካሄዱ የጥራት ማሻሻያና የደረጃዎች ሥራ ጥረቶች ድጋፍ ለመስጠት የፍተሻ ላቦራቶሮችን ማቋቋምና ማካሄድ፣
፰. ወደፊት የሚወሰን ቅርጽና አንደ አስፈላጊነቱ ሌሎች ተጨማሪ መለያዎች የሚኖረው የጥራት ማኅተምን መወሰን፣
፱. በጥራት ማኅተም ለመጠቀም ፈቃድ መስጠት ማደስ ማገድ ወይም መሰረዝ፣
፲. መርቶች እና/ወይም ሂደቶች አግባብነት ካላቸው አስገደጅ የኢትዮጵያ ደረጃዎች ጋር ተስማሚ ካልሆኑ በቅድሚያ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ፋብሪካዎች ወይም የንግድ ተቋሞች እንዲዘጉ ወይም ሥራቸውን እንዲቋረጥ ወይም የምርቶች እንቅስቃሴ እንዲታገድ ትዕዛራ መስጠት፣
፲፩. ጥራትንና ደረጃን የተመለከተ መረጃ ለመስጠት የሥርዓተ ሰነድና መረጃ ማዕከል ማቋቋም፣
፲፪. የጥራትንና የደረጃን አስፈላጊነትና ጠቀሜታ በተጠቃሚውና በኅብረተሰቡ ዘንድ ማስተዋወቅ፣
፲፫. የደረጃዎች ሥራን በሚመለከት ማናቸውም ጉባዔዎች ሴሚናሮች ወይም ስብሰባዎት ላይ መንፖሠትን ወክሎ መሳተፍ፣
፲፬. ተግባሩን ለማራመድ ከደረጃዎች ሥራ አካሎች ከሙያ ማኅበሮችና ከጥራት ሥራ ጋር ከተያያዙ ማኅበሮች ከሰርቲፊኬሽን አካሎችና ከሌሎች መሰል ድርጅቶች ጋር የሥራ ግንኙነት መፍጠርና መጠበቅ፣
፲፭. የኢትዮጵያ ደረጃዎችን በብቃት በሥራ ላይ ለማዋል አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ሥልጣንና ተግባሩን እንደአስፈላጊነቱ ለአገር ውስጥና ለውጭ አገር ድርጅቶች በከፊል በውክልና መስጠት፣
፲፮. ለሚሰጠው ማናቸውም አገልግሎት ዋጋ ማስከፈል፣
፲፯. የንብረት ባለቤት የመሆን ውል የመዋዋል በራሱ ስም የመክሰስና የመከሰስ፣
፲፰. ዓላማውን ከግብ ለማድረስ የሚረዱ ሌሎች ተመሳሳይ ተግባሮችን ማከናወን፡፡
፯. የባለሥልጣኑ አቋም
ባለሥልጣኑ፣
፩. የሥራ አመራር ቦርድ (ከዚህ በኋላ “ቦርዱ” የተባለ የሚጠራ)፣
፪. በመንግሥት የሚሾም አንድ ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ እና
፫. አስፈላጊው ሠራተኞች ይኖሩታል፡፡

፰. የቦርድ አባላት
ቦርዱ አንድ ሊቀመንበርና ቁጥራቸው ከስድስት የማይበልጥ በመንግሥት የሚሾሙ አባላት ይኖሩታል፡፡

፱. የቦርዱ ሥልጣንና ተግባር
፩. የባለሥልጣኑን የፖሊሲ ጉዳዮች ይወስናል፣ ሥራዎቹን በመንግሠት የሚሾሙ አባላት ይኖሩታል፣
፪. የባለሥልጣኑን የአጭርና የረጅም ግዜ ዕቅድ እንዲሁም ዓመታዊ የሥራ ፕሮግራምና በጀት በራሱ ደረጃ ያጸድቃል፣ በተግባር መተርጐሙን ያረጋግጣል፣
፫. የባለሥልጣኑን ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸመ ሪፖርት ያጸድቃል፣
፬. የኢትዮጵያ ደረጃዎችን ያጸድቃል፣
፭. ባለሥልጣኑ ለሚሰጠው የጥራት ማኅተም ክፍያ እና ሌሎች የአገልግሎቶች ክፍያዎችን ይወስናል፣
፮. እንደአስፈላጊነቱ የፖሊሲ አማካሪ ኮሚቴዎች ያቋቁማል፣
፯. በዋና ሥራ አስኪያጁ በሚቀርቡ የባለሥልጣኑን አስተዳደርና አመራር በሚመለቱ ሌሎች ጉዳዮች ላየ ይወስናል፡፡

፲. የቦርዱ ስብሰባ
፩. ቦርዱ ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ይሰበሰባል፡፡
፪. በቦርዱ ስብሰባ ላይ አብዛኞቹ አባላት ከተገኙ ምልዐተ ጉባዔ ይሆናል፡፡
፫. የቦርዱ ውሳኔ የሚተላለፈው ከአባሎቹ በአብዛኛው ድምጽ ሲደገፍ ይሆናል፣ ሆኖም ድምጹ እኩል የተከፈለ እንደሆነ ሰብሳቢው ወሳኝ ድምጽ ኖረዋል፡፡
፬. የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው፣ ቦርዱ የራሱን የስብሰባ ሥነ ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል፡፡

፲፩. የዋናው ሥራ አስኪያጅ ሥልጣንና ተግባር
፩. ዋናው ሥራ አሰኪያጅ የባለሥልጣኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ከቦርዱ በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሠረት የባለሥልጣኑን ሥራ ያቅዳል፣ ያስተዳድራል፡፡
፪. የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (፩) አጠቃላይ ሃሣብ እንደተጠበቀ ሆኖ ዋናው ሥራ አስኪያጅ፣
ሀ. በዚህ አዋጅ አንቀጽ ፮ ላይ የተጠቀሰውን የባለሥልጣኒን ሥልጣንና ተግባር ሥራ ላይ ያውላል፣
ለ. የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ሕግን መሠረታዊ መርሆዎች ተከትሎ ቦርዱ በሚያጸድቀው መመሪያ መሠረት የባለሥልጣኑን ሠራኞች ይቀጥራል፣ ያስተዳድራል፣
ሐ. የባለሥልጣኑን የሥራ ፕሮግራምና በጀት ያዘጋጃል፣ ሲፈቀድም በሥራ ላይ ያውላል፣
መ. ለባለሥልጣኑ በተፈቀደው በጀት መሠረት ገንዘብ ወጪ ያደርጋል፣
ሠ. ባለሥልጣኑ ከሦስተኛ ወገኖች ጋር በማያደርገው ግንኙነቶች ሁሉ ባለሥልጣኑን ይወክላል፣
ረ. የባለሥልጣኑን የሥራ እንቅስቃሴና ሂሣብ ሪፖርት አዘጋጅቶ ያቀርባል፡፡
፫. ዋናው ሥራ አስኪያጅ ለባለሥልጣኑ የሥራ ቅልጥፍና ባስፈለገ መጠን ከሥልጣኑና ተግባሩ በከፊል ለባለሥልጣኑ ሌሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች በውክልና ሊጥ ይችላል፡፡

፲፪. ስለ በጀት
የባለሥልጣኑ በጀት ከሚከተሉት ምንጮች የተውጣጣ ይሆናል፣
፩. በመንግሥት ከሚሰጥ የበጀት ድጋፍ፣
፪. ከሚሰበሰበው የአገልግሎት ክፍያ፣ እና
፫. ከሌሎች ምንጮች ከሚገኝ ገቢ፡፡

፲፫. ስለሂሣብ መዛገብት አያያዝ
፩. ባለሥልጣኑ የተሟላና ትክክለኛ የሆኑ የሂሣብ መዛግብት ይይዛል፡፡
፪.የባለሥልጣኑ የሂሣብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ፡፡

፲፬. ስለቅጣት
በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ የበለጠ ቅጣት የሚያስቀጣ ካልሆነ በስተቀር፣
፩. ማንኛውም የባለሥልጣኑ ሹም ወይም ሠራተኞች፣
ሀ. በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ መደለያ ወይም ሌላ ጥቅም በመቀበል ወይም በዝምድና ግንኙነት በሐሰተኛና በተጭበረበረ ማስረጃ ላይ ከመስርቶ ሆነ ብሎ ወይም በቸልተኝነት የአንድን ምርት ወይም ሂደት ጥራት ወይም ደረጃ በተመለከተ ሐሰተኛ የምስክር ወረቀት ወይም ማረጋገጫ የሰጠ ወይም እንዲሰጥ ያደረገ እንደሆነ ወይም፣
ለ.መደለያ ወይም ሌላ ጥቅም በመፈለግ ወይም ሰወን ለመጉዳት በማሰብ በኃላፊነቱ የቀረበለትን ውሳኔ ወይም ጉዳይ በወቅቱ ባለመፈጸም ባለጉዳዩን ያጉላላ እንደሆነ፣
በመደለያ የተቀበለውን ገንዘብ ሦስት እጥፍ ያልበለጠና፣ ከ፲ ዓመት በማያንስ እና ከ፲፭ በማይበልጥ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
፪.   የኢትዮጵያ የደረጃዎችን ሥራ በሥራ ላይ እንዲውል ከባለሥልጣኑ ውክልና ወይም ሥልጣን የተሰጠው ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት፣
ሀ. በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ መንገድ መደለያ ወይም ሌላ ጥቅም በተመቀበለ ወይም በራምድና ግንኙነት በሐተሰኛና በተጭበረበረ ማስረጃ ላይ ተመስርቶ ሆኘ ብሎ ወይም በቸልተኝነት የአንድን ምርት ወይም ሂደት ጥራት ወይም ደረጃ በተመለከተ ሐተሰኛ የምስክር ወረቀት ወይም ማረጋገጫ የሰጠ ወይም እንዲሰጥ ያደረገ እንደሆነ ወይም
ለ. መደለያ ወይም ሌላ ጥቅም በመፈለግ ወይም ሰውን ለመጉዳት በማሰብ በኃላፊነቱ የቀረበለትን ውሳኔ ወይም ጉዳይ በወቅቱ ባለመፈጸም ባለጉዳዩን ያጉላላ እንደሆነ፣ በመደለያ የተቀበለውን ገንዘብ ሦስት እጥፍ ያልበለጠ እና ከ፲ ዓመት በማያንስ እና ከ፲፭ ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፣ እንዲሁም የተሰጠው ውክልና ወይመ ሥልጣን ይሠረዝበታል፡፡
፫. ማንኛውም ሰው፣
ሀ. በአንድ ምርት ወይም ሂደት ላይ የማጭበርበር ድርጊት እንዲፈጸም መደለያ ወይም ሌላ ስጦታ የሰጠ ወይመ ለመስጠት የሞከረ እንደሆነ በመደለያ የሰጠውን ወይም ለመስጠት ያቀረበውን ገንዘብ ሦስት እጥፍ ያልበለጠ መቀጮ እና ከ፲ ዓመት በማያንስ እና ከ፲፭ ዓመት በማይበልጥ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
ለ. የጥራት ማኅተም ፈቃድ፣ ወይም የተስማሚነት የምስክር ወረቀት ሳይኖረው አንድ አስገደጅ የኢትዮጵያ ደረጃ ያለውን ምርት ወይመ የመለኪያ መሣሪያ የሸጠ ወይም ለሸይጭ ያቀረበ እንደሆነ ከ፫ ዓመት ባልበለጠ እሥሪትና ከብር ፲ሺ ባልበለጠ መቀጮ ይቀጣል፣ የተፈጸመው ድርጊት በሰው ሕይወት ወይመ ጤንነት ላይ ወይም በኢኮኖሚው ላይ ጉልህ ጉድለት ያደረሰ እንደሆነ ቅጣቱ እስከ ፲፭ ዓመት ጽኑ እሥራትና እስከ ብር ፲ሺ መቀጮ ሊደርስ ይችላል፡፡
ሐ. ወቀታዊ ካሊብሬሽን ማረጋገጫ የሚያስፈልጋቸውን የመለክያ መሣሪያዎች ያለምስክር ወረቀት የተጠቀመ ከ፫ ዓመት ባልበለጠ እሥራትና ከብር ፲ሺህ ባልበለጠ መቀጮ ይቀጣል፣ የተፈጸመው ድርጊት በሰው ሕይወት ወይም ጤንነት ላይ ወይም በኢኮኖሚው ላይ ጉልህ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ ቅጣቱ እስከ ፲ ዓመት ጽኑ እሥራትና እስከ ብር ፳ሺህ መቀጮ ሊደርስ ይችላል፡፡
መ. የተስማሚነት የምስክር ወረቀት ወይመ የጥራት ማኅተም ተሰጥቶት የምስክር ወረቀቱን ወይም ማኅተሙን በፈቃዱ ላይ ከተመለከተው ሁኔታ ውጭ የተጠቀመ ወይም ፈቃዱ ከተሰረዘ በኋላ አገልግለት መስጠቱን የቀጠለ ከ፫ ዓመት ባልበለጠ እሥራትና ከብር ፲ሺህ ባልበለጠ መቀጮ ይቀጣል፡፡
ሠ. በሐሰት ኢንስፔክተር ነኝ ብሎ እራሱን ያቀረበ ወይም ኢንስፔክተሩ ተግባሩን በሚያከናውንበት ወቅት እንቅፋት ወይም መሰናክል የሆነ እንደሆነ ከ፫ ዓመት ባልበለጠ እሥራት ይቀጣል፡፡
ረ. ስለቅድመ እሽግ የወጣውን ደንብ ባለመከተል የቅድመ እሽግ የሸጠ እንደሆነ ከ፩ ዓመት ባልበለጠ እሥራትና ከበር ፭ሺህ ባልበለጠ መቀጮ ይቀጣል፡፡
፬. በዚህ አንቀጽ ንዑስ (፩) (ሀ)፣ (፪) (ሀ) እና (፫) (ሀ) የተመለከቱትን የወንጀል ድርጊቶች በመፈጸመ ተግባር ውስጥ የተሳተፈ እና ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት ስለተፈጸመው ጥፋትና ስለተባባሪዎቹ ሚና ጠቃሚ መረጃ የሰጠን ሰው የፍትሕ ሚኒስቴር በዚህ ሕግ መሠረት እንዳይከሰስ ሊያደርግ ይችላል፡፡

፲፭. የተሻሩና ጸንተው የሚቆዩ ሕጐች
፩. የኢትዮጵያ ደረጃዎች መዳቢ ባለሥልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር ፫፻፳፰/፲፱፻፹ እና የሚዛንና የመስፈሪያ አወጅ ቁጥር ፪፻፰/፲፱፻፶፭ በዚህ አዋጅ ተሽረዋል፡፡
፪. የደረጃዎች ማኅተም እና የአገልግሎት ዋጋ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጠር ፲፫/፲፱፻፹፪፣ የሚዛንና የመስፈሪያ ደንብ ቁጥር ፬፻፴፩/፲፱፻፷፭  የኢትዮጵያ ደረጃዎች የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፪/፲፱፻፹፪ በሌላ ሕግ እሰኪተኩ ድረስ እንደጸኑ ይቆያሉ፡፡

፲፮. አግባብነት የሌላቸው ሕጐች
ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረኑ ማናቸውም ሕጐች በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖራቸውም፡፡

፲፯. መብትና ግዴታ ስለማስተላለፍ
በአዋጅ ቁጥር ፫፻፳፰/፲፱፻፹ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ደረጃዎች መዳቢ ባለሥልጣን መብትና ግዴታዎች በዚህ አዋጅ ለባለሥልጣኑ ተላልፈዋል፡፡

፲፰. የመተባበር ግዴታ
ማንኛውም ሰው ለዚህ አዋጅ አፈጻጸም የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡

፲፱. አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ
ይህ አዋጅ ከየካቲት ፳፫ ቀን ፲፱፻፺ ዓ.ም.

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ፕሬዚዳንት