አዋጅ ቁጥር ፻/፲፱፲፻፺ ዓ.ም. የሕፃናት መብቶች ኮንኬሽን አንቀጽ ፵፫(፪) ማሻሻያን ማጽደቂያ አዋጅ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

አዋጅ ቁጥር ፻/፲፱፲፻፺ ዓ.ም. የሕፃናት መብቶች ኮንኬሽን አንቀጽ ፵፫(፪) ማሻሻያን ማጽደቂያ አዋጅ

አዋጅ ቁጥር ፻/፲፱፻፺
የሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን አንቀጽ ፵፫(፪)ን ማሻሻያ ለማጽደቅ
የወጣ አዋጅ

ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ባጸደቀችው የሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን አንቀጽ ፵፫(፪) ላይ በኮንቬንሽኑ አባል ሀገሮች ጉባዔ እ.ኤ.አ. ዲሴምበር ፲፪ ቀን ፲፱፻፹፯ የተደረገውን ማሻሻያ ከደገፉት አንዷ በመሆኗ፣
በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ዲሴምበር ፳፩ ቀን ፲፱፻፹፯ ተቀባይነት የተሰጠው ማሻሻያ የሚጸና፣ ኮንቬንሽኑ አባል ሀገሮች ሁለት ሦስተኛው በኮንቬንሽኑ አንቀጽ ፶(፪) መሠረት ሲያጸድቁት ጭምር ስለሆነ፣
ይህንኑ ማሻሻያ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት ፲፭ ቀን ፲፱፻፺ ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ያጸደቀው ስለሆነ፣
በሕገመንግሥቱ አንቀጽ ፶፭ ንዑስ አንቀጽ (፩) እና (፪) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

፩. አጭር ርዕስ
ይህ አዋጅ “የሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን ማሻሻያን ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር ፻/፲፱፻፺”  ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ማሻሻያው ስለመጽደቁ
የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ዲሴምበር ፳፩ ቀን ፲፱፻፺፭ ዓ.ም. የተቀበለው በሕፃናት መብቶች ኮንቬንሽን አንቀጽ ፵፫(፪)  ላይ የተደረገ ማሻሻያ ጸድቋል፡፡

፫. አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ

ይህ አዋጅ ከየካቲት ፲፮ ቀን ፲፱፻፺ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ የካቲት ፲፮ ቀን ፲፱፻፺ ዓ.ም.
ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ፕሬዚዳንት