የፍርድ ቤቶች ሥልጣን የዐቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤትና ፖሊስ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

የፍርድ ቤቶች ሥልጣን የዐቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤትና ፖሊስ

አንደኛ መጽሐፍ፡፡
የፍርድ ቤቶች ሥልጣን የዐቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤትና ፖሊስ
ምዕራፍ ፩
የፍርድ ቤቶች ሥልጣን፡፡

 ቍ ፬፡፡ ወንጀልን ስለሚመለከት ሥልጣን

(፩)  በአንደኛው ሠንጠረዥ በሦስተኛው ዐምድ ሠንጠረዥ የተገለጹት ፍርድ ቤቶች በመጀመሪያውና በሁለተኛው ዐምዶች የተገለጹትን ወንጀሎች ለማየትና ሕጉ የሚያዘውን ቅጣት ለመፍረድ ሥልጣን አላቸው፡፡
(፪)  የፍርድ ሚኒስትር በነጋሪት ጋዜጣ በሚወጣ ትእዛዝ በአንደኛው ሠንጠረዥ ለመለወጥ ወይም ለማሻሻል ይችላል፡፡

ቍ ፭፡፡ ስለሚከሰሱ ሰዎች፡፡

(፩)  በወንጀለኛ መቅጫ ቁጥር ፶፫ እንደተመለከተው ዕድሜው ከ፱ ዓመት እስከ ፲፭ ዓመት የሆነ አካለ መጠን ያላደረሰ ልጅ ዕድሜው አካለ መጠን ከደረሰ ሰው ጋር በተከሰሱበት የወንጀል ነገር አብሮ ሊታይ አይቻልም፡፡
(፪)  በወታደር ፍርድ ቤት ሥልጣን የሚታይ ካልሆነ በቀር የጦር ሠራዊት አባልና የሲቪል ሰው አብረው ሊሞገቱ ይችላሉ፡፡

ቍ ፮:፡፡ የሥልጣኑ ክበብ፡፡

ከቍጥር ፺፱ እስከ ፻፯  በተመለከተው መሠረት ፍርድ ቤቶች በተወሰነላቸው ቦታዎች (አጥቢያዎች) የዳኝነት ሥልጣን አላቸው፡፡

ቍ ፯፡፡ የይግባኝ ሥልጣን፡፡

በቍጥር ፻፹፪ በተመለከተው መሠረት ፍርድ ቤቶች ይግባኝ የማየት ሥልጣን አላቸው፡፡