የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፸፫/፲፱፻፺፫ ወደ ውጭ አገር በሚላክ ቡና ላይ የሚከፈለውን ታክስ ለማሻሻል የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፸፫/፲፱፻፺፫ ወደ ውጭ አገር በሚላክ ቡና ላይ የሚከፈለውን ታክስ ለማሻሻል የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፸፫/፲፱፻፺፫
ወደ ውጭ አገር በሚላክ ቡና ላይ የሚከፈለውን ታክስ
ለማሻሻል የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬/፲፱፻፺ አንቀጽ ፭ እና ወደውጭ አገር በሚላክ ቡና ላይ ስለሚከፈል ታክስ በወጣው አዋጅ ቁጥር ፺፱/፲፱፻፺ አንቀጽ ፰ የታክሱን ማስከፈያ ልክ ለማሻሻል የሚያስችል ደንብ ለማውጣት በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡

፩. አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ “ወደውጭ አገር በሚላክ ቡና ላይ የሚከፈለውን ታክስ ለማሻሻል የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፸፫/፲፱፻፺፫ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ማሻሻያ
ወደ ውጭ አገር በሚላክ ቡና ላይ ስለሚከፈል ታክስ የወጣው አዋጅ ቁጥር ፺፱/፲፱፻፺ አንቀጽ ፬ ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀጽ ፬ ተተክቷል፡፡
፬. የታክሱ ማስከፈያ ልክ
፩. የታክሱ ማስከፈያ ልክ ዕቃው በሚጫንበት ጊዜ የሚሰጥ ዋጋ ፮ ነጥብ ፭ ፐርሰንት (ስድስት ነጥብ አምስት በመቶ) ይሆናል፡፡
፪. ከዚህ በላይ በንዑስ አንቀጽ (፩) የተደነገገው ቢኖርም ዕቃው በሚጫንበት ጊዜ የሚሰጠው ዋጋ፤
ሀ) የታጠበ ቡና በነጥር ከ፩፻፭ (አንድ መቶ አምስት) የአሜሪካን ሣንቲም፤
ለ) ያልታጠበ ቡና በነጥር ከ፸(ሰባ) የአሜሪካን ሣንቲም፤
በታች ከሆነ ታክስ አይከፈልበትም፡፡

፫. ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ
ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ ግንቦት ፲፮ ቀን ፲፱፻፺፫ ዓ.ም.
መለስ ዜናዊ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ጠቅላይ ሚኒስትር