ደንብ ቁጥር ፲፩/፲፱፻፹፱ ዓ.ም. የጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት (ማሻሻያ) ደንብ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

ደንብ ቁጥር ፲፩/፲፱፻፹፱ ዓ.ም. የጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት (ማሻሻያ) ደንብ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፲፩/፲፱፻፹፱
የጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ ደንብን ለማሻሻል የወጣ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬/፲፱፻፹፯ አንቀጽ ፭ እና በዓለም አቀፍ የተወሀደ የሸቀጦች አሰያየምና አመዳደብ ሥርዓት ኮንቬንሽን ማጽደቂያ አዋጅ ቁጥር ፷፯/፲፱፻፹፭ አንቀጽ ፬ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡
፩. አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ ‹‹የጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት (ማሻሻያ) ደንብ ቁጥር ፲፩/፲፱፻፹፱›› ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ማሻሻያ
ከጉምሩክ ቀረጥ ማስከፈያ ደንብ ቁጥር ፻፳፪/፲፱፻፹፭ (እንደተሻሻለ) ጋር ተያይዞ የሚገኘው የጉምሩክ የዕቃ ቀረጥ ሥርዓትና ተመን እንደገና ከዚህ ደንብ ጋር ተያይዞ በሚገኘው ሠንጠረዥ ተሻሽሏል፡፡

፫. ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ
ይህ ደንብ ከታኅሣሥ ፲፰ ቀን ፲፱፻፹፱ ዓ.ም. ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡
አዲስ አበባ ታኅሣሥ ፲፰ ቀን ፲፱፻፹፱ ዓ.ም.

መለስ ዜናዊ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ጠቅላይ ሚኒስትር