የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፮/፲፱፻፺ ዓ.ም. የኢንቨስትመንት ማበረትቻ የሚኒስትሮች ምክር ቤት (ማሻሻያ) ደንብ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፮/፲፱፻፺ ዓ.ም. የኢንቨስትመንት ማበረትቻ የሚኒስትሮች ምክር ቤት (ማሻሻያ) ደንብ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፮/፲፱፻፺
የኢንቨስትመንት ማበረታቻ ደንብን ለማሻሻል የወጣ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬/፲፱፻፹፯ አንቀጽ ፭ እና በኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር ፴፯/፲፱፻፹፰ (እንደተሻሻለ) አንቀጽ ፱ መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡

፩. አጭር ርዕስ
የህ ደንብ “የኢንቨስትመንት ማበረታቻ የሚኒስትሮች ምክር ቤት (ማሻሻያ) ደንብ ቁጥር ፴፮/፲፱፻፺” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ማሻሻያ
የኢንቨስትመንት ማበረታቻ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፯/፲፱፻፹፰ እንደተመለከተው ተሻሽሏል፤
፩. የደንቡ አንቀጽ ፮ ንዑስ አንቀጽ (፪) ተራ ፊደል (ሀ) ተሠርዞ በሚከተለው አዲስ ተራ ፊደል (ሀ) ተተክቷል፡፡
ሀ. ካፒታሉ እስከ ብር ፪ ሚሊዮን ሲሆን … ፵፭%፣ ሆኖም ለማስፋፊያ ወይም ለማሻሻያ ፕሮጀክቱ የተመደበው የኢንቨስትመንት ካፒታል የድርጅቱን ጠቅላላ የኢንቨስትመንት ካፒታል ቢያንስ ወደ ብር ፪፻፶ ሺህ ከፍ ማድረግ አለበት”
፪. የደንቡ አንቀጽ ፲፩ ንዑስ አንቀጽ (፬)፣ (፭) እና (፮) ተሠርዘው በሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀጽ (፬) እና (፭) ተተክተዋል፤
“፬. ማናቸውም የካፒታል ዕቃዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቅዳል፡፡ ሆኖም ከውጭ የሚገቡትን ሊተኩ የሚችሉ የካፒታል ዕቃዎችና መሣሪያዎት በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ከሆነ ከውጭ የሚገቡት ከቀረጥ ነፃ ሆነው እንዳይገቡ ቦርድ በየጊዜው በሚያወጣው መመሪያ ሊያግድ ይችላል፡፡
“፭. ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆኖ የገባ ማናቸውም ዕቃ ሊከፈልበት ይገባ የነበረው የጉምሩክ ቀረጠ አስቀድሞ ሳይከፈልበት የቀረጥ ነፃ መብት ለሌለው ሰው ሊተላለፍ አይችልም፡፡”
፫. ከደንቡ አንቀጽ ፳፪ በኋላ የሚከተሉት አዲስ አንቀጾች ፳፫፣ ፳፬፣ ፳፭፣ ፳፮ እና ፳፯ ተጨምረዋል፤
“፳፫. ለመከላከያ ኢንድስትሪ ኢንቨስትመንት የሚፈቀዱ መሣሪያዎች
በዚህ ደንብ አንቀጽ ፲፫ (እንደተሻሻለ) የተደነገገው ለመከላከያ ኢንዱስትሪም ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
፳፬ . ለኢንዱስትሪ መንደር ኢንቨስትመንት የሚፈቀዱ መሣሪያዎች
ለኢንዱስትሪ መንደር የሚያስፈልጉ መሣሪያዎችና ዕቃዎች እንዲሁም በቀጥታ ለኢንዱስትሪ መንደር ሕንፃ ግንባታ የሚያገለግሉ በሀገር ውስጥ የማይመረቱ መማሪያዎችና ማቴሪያሎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል፡፡
፳፭. ለቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት ኢንቨስትመንብ የሚፈቀዱ መማሪያዎች
ለቴሌኩሙኒኬሽን አገልግሎት የሚያስፈልጉ ቋሚ መሣሪያዎችና ዕቃዎች በዋጋ ከ፲፭% ከማይበልጥ የመለዋወጫ ዕቃዎች ጋር ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል፡፡
፳፮. ለምርምርና ስርዐት ኢንቨስትመንት የሚፈቀዱ መሣሪያዎች
ለምርምና ስርዐት ኢንቨስትመንት የሚያስፈልጉ ቋሚ ዕቃዎችና መሣሪያዎች ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል፡፡
፳፯. ለካፒታል ዕቃዎች ኪራይ አገልግሎት የሚፈቀዱ መማሪያዎች
በዚህ ደንብ አንቀጽ ፲፫፤ ፲፰-፳፪ የተመለከቱትን እንዲሁም ለማዕድንና ለፔትሮሊየም ሥራዎች እንደ ካፒታል ዕቃ የሚያገለግሉ መሣሪያዎችን ለኪራይ አገልግሎት ለማዋለ ከጉምሩክ ቀረጥ ነፃ ሆነው እንዲገቡ ይፈቀዳል፡፡”
፬. የደንቡ አንቀጽ ፳፫፣ ፳፬ እና ፳፭ እንደ ቅደም ተከተላቸው አንቀጽ ፳፰፣ ፳፱ እና ፴ ሆነዋል፡፡
፭. በደንቡ ሠንጠረዥ አንድ ተራ ፊደል “መ” ሥር የሚከተሉት አዲስ ተራ ቁጥር ፶ እና ፶፩ ተጨምረዋል፣
“፶. የመከላከያ ኢንዱስትሪ (፪ሺ፱፻፳፯)፣
፶፩. የኢንዱስትሪ መንደር (፯ሺ፲)፡፡”
፮. በደንቡ ሠንጠረዥ አንድ ሥር የሚከተሉት አዲስ ተራ ፊደል “ረ”፣ “ሰ”፣ “ሸ” እና “ቀ” ተጨምረዋል፤
“ረ. የቴሌኮሙኒኬሽን አገልግሎት (፮ሺ ፬፻፳)፣
ሰ. ምርምርና ስርዐት (፯ሺ፫፻፲፣፯ሺ፫፻፳)፡፡”
ሸ. ትምህርት
፩. ጠቅላላ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት (፹ሺ ፪፻፲)
፪. የሁለተኛ ደረጃ የቴክኒክና የሙያ ትምህርት (፹ሺ ፪፻፳፣፹ሺ ፱፻፩)
፫. ከፍተኛ ትምህርት (፹ሺ፫፻)
ቀ. ጤና
፩. ሆስፒታሎች (፹፭ሺ ፻፲) (ከአዲስ አበባ ውጭ ሲሆን)
፪. የዲያግኖስቲክ ምርመራ ማዕከሎች (፹፭ሺ ፻፺) (ከአዲስ አበባ ውጭ ሲሆን)”
፯. የደንቡ ሠንጠረዥ ሁለት ተራ ፊደል “ረ” ተራ ቁጥር ፫፣ ፬ እና ፭ ተሠርዘዋል፡፡
፰. የደንቡ ሠንጠረዥ ሁለት ተራ ፊደል “ሰ” ተተክቷል፡፡
“ሰ. ጤና
፩. ሆስፒታሎች (፹፭ሺ ፻፲) (አዲስ አበባ ውሰጥ ሲሆን)
፪. የጤና ጣቢያዎች (፹፭ሺ ፻፳)
፫. የዲያግኖስቲክ የምርመራ ማዕከሎች (፹፭ሺ፻፺) (በአዲስ አበባ ውስጥ ሲሆን)
፬. ክሊኒኮች (፹፭ሺ ፻፳)“
፭. በንቡ ሠንጠረዥ ሦሰት ሥር የሚከተለው አዲስ ተራ ፊደል “ሰ” ተጨምሯል፤
“ሰ. የካፒታል ዕቃ ኪራይ አገልግሎት (፸፩ሺ ፲፪፣ ፸፩ሺ ፲፫፣ ፸፩ሺ ፳፱)፡፡”
አዲስ አበባ ሰኔ ፭ ቀን ፲፱፻፺ ዓ.ም.
መለስ ዜናዊ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ጠቅላይ ሚኒስትር