የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፭/፲፱፻፺ ዓ.ም. ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ስለተከለሉ የሥራ መሰኮች የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፭/፲፱፻፺ ዓ.ም. ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ስለተከለሉ የሥራ መሰኮች የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፭/፲፱፻፺
ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ስለተከለሉ የሥራ መስኮች
የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላል ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካለትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፬/፲፱፻፹፯ አንቀጽ ፭ እና በኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር ፴፯/፲፱፻፹፰ (እንደተሻሻለ) አንቀጽ ፮(፪) መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡

፩. አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ “ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች ስለተከለሉ የሥራ መስኮች የወጣ የማኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፭/፲፱፻፺” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. ትርጓሜ
በዚህ ደንብ ውስጥ “የአገር ውስጥ ባለሀብት” ማለት በኢንቨስትመንት አዋጅ ቁጥር ፴፯/፲፱፻፹፰ (እንደተሻሻለ) አንቀጽ ፪(፭) የተመለከተው ትርጓሜ ይኖረዋል፡፡

፫. ለአገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለሉ የሥራ መስኮች
ከዚህ ደንብ ጋር ተያይዞ በማገኘው ሠንጠረዥ የተመለከቱት የሥራ መሰኮች በአገር ውስጥ ባለሀብቶች ብቻ የሚካሄድ ይሆናሉ፡፡

፬. ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ
ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ይሆናል፡፡
አዲስ አበባ ሰኔ ፭ ቀን ፲፱፻፺ ዓ.ም.

መለስ ዜናዊ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ
ጠቅላይ ሚኒስትር

ሠንጠረዥ
ለሀገር ውስጥ ባለሀብቶች የተከለሉ የሥራ መስኮች
፩. የፌዲዮና የቴሌቪዥን ሥርጭት አገልግሎት፣
፪. የችርቻሮ ንግድና የድለላ ሥራ፤
፫. የጅምላ ንግድ (ነዳጅና የነዳጅ ምርቶችን ማቅረብ እንዲሁም የውጭ ባሀብቶች በአገር ውስጥ ያመረቱን በጅምላ መሸጥን ሳይጨምር)፤
፬. የገቢ ንግድ፤
፭. ጥሬ ቡና፣ የቅባት እህሎችን፣ ጥራጥሬ፣ ቆዳና ሌጦ እንዲሁም ኢንቨስተሩ ራሱ ካረባቸው ወይም ካደለባቸው በስተቀር በጐችን፣ ፍየሎችን፣ የቀንድ ከብቶችን በቁም ወደ ውጭ መላክ፣
፮. ደረጃ አንድ ከሚመደቡት በስተቀር የኮንሰትራክሽን ሥራ ተቋራጭነት፤
፯. ቆዳና ሌጦ እስከ ክረስት ደረጃ ማልፋት፤
፰. የባለኮከብ ደረጃዎችን የማይጨምሩ ሆቴሎች፣ ሞቴሎች፣ ፔንሲዮኖች፣ ሻይ ቤቶች፣ ቡና ቤቶችና መጠጥ ቤቶች፣ የምሽት ክበቦች፣ ዓለም አቀፋዊ ይዘት ካላቸውና በተወሰነ አገር ምግብ አዘገጃጀት ከሚታወቁት በስተቀር ሌሎች ምግብ ቤቶች፣
፱. የማስጐብኘት አገልግሎት፣ የጉዞ ወኪልነት የኮሚሲዮን ወኪልነትና የቲኬት መሸጫዎች፤
፲. መኪና የማከራየትና የታክሲ አገልግሎት፤
፲፩. የመንገድ የንግድ ተራንስትፖርት አገልግሎትና የሀገር ውስጥ ውሃ ላየ ትራንስፖርት አገልግሎት፤
፲፪. ለሀገር ውስጥ ገበያ ብቻ የሚቀርቡ የዳቦና የኬክ ምርቶች፤
፲፫.  ወፍጨ ቤቶች፤
፲፬. ፀጉር ማስተካከል፣ የቁንጅና ሳሎን፣ የአንጥረኝነት ሥራ በፋብሪካ ደረጃ የማይካሄድ የልብስ ስፌት፤
፲፭. የሕንፃ እድሳትና የመኪና ጥገና አገልግሎት፤
፲፮. የእንጨት መሰንጠቂያና የጣውላ ሥራዎች ፣ እንዲሁም ለሀገር ገበያ ብቻ የሚቀርቡ የእንጨት ሥራ ውጤቶችን ማምረት፤
፲፯. የጉመሩክ አስተላላፊነት ሥራ፤
፲፰. የሙዚየም፣ የቲያትርና የሲኒማ ማሣየት አገልግሎት፤
፲፱. የሕትመት ሥራ፤
፳. ባሕላዊ የማዕድን ሥራ፡፡