የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፩/፲፱፻፺ ዓ.ም. የሻይ ልማትና ገበያ ድርጅትን ለማፍረስ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፩/፲፱፻፺ ዓ.ም. የሻይ ልማትና ገበያ ድርጅትን ለማፍረስ የወጣ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፩/፲፱፻፺

የሻይ ልማትና ገበያ ድርጅትን ለማፍረስ የወጣ የሚኒስትሮች
ምክር ቤት ደንብ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ አስፈጻሚ አካላትን ሥለጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አወጅ ቁጥር ፬/፲፱፻፹፯ አንቀጽ ፭ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር ፳፭/፲፱፻፹፬ አንቀጽ ፵፯ /፩/ሐ መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡

፩. አጭር ርዕስ
ይህ ደንብ “የሻይ ልማትና ገበያ ድርጅት ማፍረሻ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፴፩/፲፱፻፺” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

፪. መፍረስ
በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፻፶፪/፲፱፻፹፭ ተቋቁሞ የነበረው የሻይ ልማትና ገበያ ልማትና ገበያ ድርጅት በዚህ ደንብ ፈርሷል፡፡

፫. መብትና ግዴታና ስማስተላለፍ
በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፻፶፪/፲፱፻፹፭ ተቋቁሞ የነበረው የሻይ ልማትና ገበያ ድርጅት መብትና ግዴታዎች ለሚከተሉት ድርጅቶች ተላልፈዋል፡፡
፩. በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፰/፲፱፻፺ ለተቋቋመው የሻይ ምርትና ገበያ ድርጅት፣
. በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር ፳፱/፲፱፻፺ ለተቋቋመው የጉማሮ ሻይ ልማት ድርጅት፣
. በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ  ቁጥር ፴/፲፱፻፺ ለተቋቋመው የውሽውሽ ሻይ ልማት ድርጅት፡፡

፬. ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ
ይህ ደንብ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትመ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸና የሆናል፡፡

አዲስ አበባ የካቲት ፲፫ ቀን ፲፱፻፺ ዓ.ም.
መለስ ዚናዊ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ