በወንጀል ነገር የሚከፈል የኪሣራ ወጪ | GOALGOOLE | Because you need Information for your goals !
7023 Bole Kifle Ketema, Addis Ababa, Ethiopia
0116616179/85 mcc@ethionet.et

በወንጀል ነገር የሚከፈል የኪሣራ ወጪ

ሰባተኛ መጽሐፍ፡፡
በወንጀል ነገር የሚከፈል የኪሣራ ወጪ፡፡

ቍ ፪፻፳፡፡ ዐቃቤ ሕጉ ለሚያቀርበው ክስ የኪሣራ ወጪ፡፡

(፩)     በዐቃቤ ሕግ በኩል ለሚቀርበው ክስ የኪሣራ ወጪ በሙሉ ከይግባኙ ጭምር መንግሥት ኃላፊ ነው፡፡
(፪)     በተፈረደበት ሰው ምክንያት በዐቃቤ ሕጉ በኩል የቀረበው ክስ የተለየ የኪሣራ ወጪ የሚደረግ እንደ ሆነና የተፈረደበት ሰው ንብረት ያለው እንደ ሆነ፤ በሕግ ከሚወሰንበት ቅጣት በላይ የፍርድ ቤቱ የመዝገብ ቤት ሹም የሚወስነውን የኪሣራ ወጪ በሙሉ ወይም በከፊል እንዲከፍል ፍርድ ቤቱ ሊያዝ ይችላል፡፡
(፫)     በአቤቱታ በሚቀርብ ክስ በዐቃቤ ሕግ በኩል ክሱ ከቀረበ በኋላ የተበደለው ሰው አቤቱታውን የተወ እንደሆነ (በወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ቍ ፪፻፳፩) መሠረት ለወንጀሉ ክስ ለተደረገው የኪሣራ ወጪ ሁሉ ኃላፊ ይሆናል፡፡

ቍ ፪፻፳፩፡፡ የግል ክስ የኪሣራ ወጪ፡፡

(፩)     በግል ክስ በሚቀርቡ ነገሮች ላለው የኪሣራ ወጪ ሁሉ በቍ ፵፮ መሠረት የግል ከሳሹ ኃላፊ ነው፡፡
(፪)     በግል ክስ ቀርቦ ተከሳሹ ነጻ የተለቀቀ እንደ ሆነና ክሱ የቀረበው በቅን ልቡና አለመሆኑን ፍርድ ቤቱ የተገነዘበ እንደ ሆነ ተከሳሹ ያወጣውን የኪሣራ ወጪ በሙሉ ወይም በከፊል የግል ከሳሹ እንዲከፍል ፍርድ ቤቱ ለማዘዝ ይችላል፡፡
(፫)     የግል ክሱ በቍ ፵፰ መሠረት የታገደ እንደሆን፤ ለግል፤ ክሱ፤ የኪሣራ ወጪ ሁሉ መንግሥት ኃላፊ ነው፡፡

ቍ ፪፻፳፪፡፡ የተበደለው ወገን፡፡

 (፩) የተበደለው ወገን በወንጀል ነገር ውስጥ ካሣ እንዲከፈለው የጠየቀ እንደሆን ከዚህ የሚከተሉትን መፈጸም አለበት፡፡
(ለ)  ምስክሮችና በምስክርነት ቃላቸውን የሚሰጡትን ልዩ ዐዋቂዎች ለመጥራት አስፈላጊውን ወጪ ይከፍላል፡፡
(፪)  የተበደለው ወገን ካሣ እንዲያገኝ የተፈረደለት እንደሆነ በንኡስ ቍ ፩ የተጠቀሰውን የኪሣራ ወጪና የዳኝነት ተከሳሹ እንዲከፍል ፍርድ ቤቱ ያዛል፡፡